ምክክሩ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የ ተሳታፊ ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ተናገሩ፡፡

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ 41 ወረዳዎች እና 16 ከተማ አስተዳደሮች በሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን እየተካሄደ ባለዉ የአጀንዳ አሰባሰብ መድረክ ከየማህበራዊ መሠረቶች እየተሳተፉ ያሉት ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክሩ፣ ሀገር ካገበችበት ውስብስብ ችግሮች ለማላቀቅ ጉሊህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል ።

በዉይቱ በመሳተፋቸው ደስተኛ ስለመሆናቸውና ምክክሩ ለሴቶች እጅግ በጣም ጠቃሚ መሆኑን የገለጹት የሴቶች ተወካይ አበዛሽ ዘውዴ፣ ምክክሩ ሀገራችንን የሚታዩ የሀሳብ ልዩነቶችን በመደማመጥና በውይይት በመፍታት ወደምንፈልገው የጋራ የሚያደርገውን ሀሳብ ለመድረስ የሚጠቅም በመሆኑ ለሀገራችን ወሳኝ ና አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ለሀገራችን አጀንዳዎችን ለማሰባሰብ ምክክር እያደረገን እንገኛለን ያሉት ወ/ሮ አበዛሽ ዘውዴ ፣ ሀገራዊ ምክክሩ ሀገር ካገበችበት ውስብስብ ችግሮች ለማላቀቅ ጉሊህ ሚና እንዳለው ገልጻዋለች።

አንተሰው አብደላ መሃመድ ከካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ የተሳተፉ አካል ጉዳተኛ ተወካይ ሲሆኑ፣ በምክክር ሂደቱ ለሀገራችን ትልቅ ተስፋ ሰጪ፣ በማያግባባን ጉዳዮች ላይ የሚያግባባ በመሆኑ ምክክሩ በዚህም ለሀገሪቱ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ያሉት።

ማህበረሰባችንን ወክለን የተገኘን ሁላችንም በሚያናጋግረን አጀንዳዎች ላይ እንደሀገር የጋራ አንድ በሚያደርጉ ነገሮቻችን ላይ አተኩረን ከሰራን ከችግር ወጥተን ማምጣት ይቻላል ብለዋል።

ከምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ የተሳፈችሁ ወ/ሮ ዘምዘም አሊና ከዳውሮ ዞን የተሳተፉ ሴቶች ተወካይ ወ/ሮ ብርቱካን ዛውዴ በበኩላቸው ሀገራዊ ምክክሩ ከዚህ በፊት ሴቶችን በሚመለከት የነበሩ ችግሮች በንግግር በውይይት እንዲፈታ የራሳችንን አጀንዳ ለማዋጣት ሲሆን በዚህም ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮች እንዲፈቱ አጋዥ ነው ብለዋል።

ሌላኛው ወጣት አንድነት ገዛኸኝ ከሸካ ዞን መድረኩ ለወጣቶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ወሳኝ ነው ያለው።

ከምዕራብ ኦሞ የተሳተፈዉ ወጣት ታምራት ብርሃኑ እና ከኮንታ ዞን ወጣት ጌታሁን መስፍን ምክክር መድረኩ ለአንድ ጤናማ ሀገር ለመገንባት ለሚደረገው ሂደት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጾ ምክክሩ በራሱ የተለያዩ ማህበረሰብ መሠረት ያካተተ በመሆኑ ልዩነቶችን በመመካከር ችግሮችን ነቅሶ ለመውጣት ጠቃሚ መሆኑን ጠቁሟል ፡፡

በሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች የነበሩ ተሳትፎዎች አስደሳች እንደነበሩና ምክክሩ በተግባር ውጤት አምጥቶ ለማየት ጉጉት እንዳላቸውም አመልክተዋል ፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *