ቼክ ሪፐብሊክ በግብርና ቴክኖሎጂ አቅርቦት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች
ቼክ ሪፐብሊክ በግብርና ቴክኖሎጂ አቅርቦት እና በእንስሳት ልማት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋገጠች፡፡ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁርካ ጋር በትብብር በሚሠሩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ባደረጉት ውይይት፤ በስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ ዐሻራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን አብራርተዋል፡፡ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማጎልበት በግብርና ሜካናይዜሽን ዘርፍ ኢትዮጵያ…
