የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሸካ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ
በጉብኝታቸውም በሸካ ዞን የኪ ወረዳ በጪ ቀበሌ በአርሶ አደሮች በክላስተር የለማ የሩዝ ምርት አሰባሰብ ሂዴትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በተደራጁ ወጣቶች በፊደና አዲስ ብርሃን ቀበሌ እየለማ የሚገኙ የቅመማ ቅመም ( ቁንዶ በርበሬ፣እርድ) ማሳም የጉብኝቱ አካል ነበሩ። ጥምር እርሻ(ሙዝ ፣ፓፓያ፣አናናስና ቡና)፣የማር መንደርን የጎበኙ ሲሆን በኩብጦ ቀበሌ የአቶ ደረጀ ዳልቶ የቡና እንዱስትሪ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል። ዶክተር ለገሰ ቱሉ በጉብኝቱ…
