
በፓናል ውይይቱ ላይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ መኮንኖች፣ የምክር ቤት አባላት፣ አርበኞችና ምሁራን ተገኝተዋል።
በኢዜአ አዲሱ ስቲዲዮ እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት የአድዋ ድል የአብሮነትና የአንድነት ተምሳሌት፣ የጥቁር ህዝቦች ነፃነት የነበረው ሚና እንዲሁም የዚህ ዘመን አድዋ ምን መሆን አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
