የ2017 በጀት ዓመት ክልላዊ ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው




የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት የምዘና ስርዓቱ ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ራዕይን እውን ለማድረግ የአመለካከት ጥራት፣የአመራር ሰጭነት ብቃት፣የታነፀ ስነ ምግባር የተላበሰ፣ በእውቀት እና በአፈፃፀም የበቁ እና የላቁ አመራርን ለመፍጠር ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር አንስተዋል።
ምዘናው እርስ በርስ መገነባባትና ውጤትን መሰረት ባደረገ፣ አሳታፊ፣ ግልጽ፣ ወጥና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ምዘናዉን በማስፈጸም የፓርቲውን አመራር ጥራትና ውጤታማነትን ማሳደግ የምዘናው ዓላማ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አመራሩ የፓርቲና የመንግስት ተልዕኮ በመፈጸምና በማስፈጸም ፣ በመመዘን ዝንፈቶችን ለማረምና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው አመራሩን በተገቢ ሁኔታ በማጥራት፣ መልሶ በማደራጀት የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን ፣የህዝቡን የመልማት ፣የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎችን፣ የመበልጸግ ፍላጎቱን ለማሳካት የሚችል የአመራር ብቃትና ዝግጁነት ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል።
መድረኩ ችግሮችን የሚፈታ ፣የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፣በየአካባቢው ያሉትን የህዝቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ህብረ ብሔራዊ አድነትን ሊያጎላ የሚችል የመገነባቢያ መድረክ መሆኑን አመላክተዋል።
የፓርቲው መርሆች ማዕከል ያደረገ እርስ በእርስ መገነባባት የሚያስችልና ወጥ የሆነ አሰራር እንዲሰፍን ከማስቻሉ በተጨማሪ የፓርቲው መርሆዎች፣ እሴቶችና አሰራሮች በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመሩ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚህም ጠንካራ የአመራር ስርዓት እውን በማድረግ ጠንካራ ፓርቲና ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር የምዘና ፋይዳው የጎላ በመሆኑ አመራሩ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የነቃ ተሳትፎና ትግል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
