





በጉብኝቱ የቦንጋ የግብርና ምርምር ማዕከል የተለያዩ የምርምር ውጤቶች የሆኑትን የሙዝ፣የዶሮ እርባታ፣የንብ ማነብ፣ችግኝ ጣቢያ፣ የእንሰሳት መኖ፣ የስራስር ምርቶች ፣እንዲሁም ሌሎች የምርምር ውጤቶችን ምልከታ ተካሂዷል።
የምርምር ማዕከላት በዘር ብዜት እና በቴክኖሎጂ በማፍለቅ ፣በተፈጥሮ ሀብት እና በእንስሳት እርባታ ማላመድና በማስተዋወቅ ረገድ ለአርሶና አርብቶ አደሮች ተደራሽ በማድረግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን በጉብኝቱ ገለጻ ተደርጓል።
በጉብኝቱ የክልሉ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የምርምር ውጤቶችን ለአርሶና አርብቶ አደር በማስፋፋትና ተደራሽ በማድረግ ይገባል ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ዓለሙ በበኩላቸው፥ በቦንጋ የምርምር ማዕከል የክልሉን ግብርና ለማዘመን የሚረዱ የተለያዩ የምርምር ውጤቶች በኤክስቴንሽን የማስፋት ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
በጉብኝቱ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩቱ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ (ዶ/ር) ሌሎች የክልሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
