ትምህርት ለትውልድ!

በክልላችን የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ በዞኑ ለጋቸብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃውን የጠበቅ 4 የመማሪያ ብሎክ ልገነባ ነው። ግንባታው ከ5.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ ይገነባል። በዞኑ “በትምህርት ለትውልድ” የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሀግብር ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦ የመማሪያ ክፍሎች እየተገነቡ እንደሚገኝ ከዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሮም ጣልያን እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የልማት እና የፍልሰት ኮንፈረንስ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ካላት ስትራቴጂካዊ አቅም አንጻር የስደት ምንጭ፣መሸጋገሪያ እና መድረሻ ነች። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ የስደት አስተዳደርን ለማጎልበት፣ ሕገ ወጥ ስደትን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመፍታት በርካታ የፖሊሲ፣ የሕግ እና ተቋማዊ ርምጃዎችን ወስዳለች። መረጃው ከጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ የተገኘ ነው። በተጨማሪም ሌሎች መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ይከታተላሉ

Read More

ፕሬዚዳንት ፑቲን የአፍሪካ የሰላም ሐሳብ ለሩሲያ-ዩክሬን ሰላም መሰረት ሊሆን ይችላል አሉ

ፕሬዚዳንት ፑቲን በአፍሪካ መሪዎች የቀረበው የሰላም ሐሳብ በሩሲያ-ዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የሰላም መሰረት ሊሆን እንደሚችል ገለጹ፡፡ ሬውተርስን ጠቅሶ አልጄዚራ እንደዘገበው የአፍሪካ መሪዎች ያቀረቡት የሰላም ዕቅድ ምንም እንኳን ሙሉ ዝርዝሩ ይፋ ባይደረግም ግጭቱን ለማርገብ ተከታታይ እርምጃዎችን ያመላከተ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል÷ የሩሲያ ጦር ወደኋላ መመለስ፣ የሩሲያ ታክቲካዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ከቤላሩስ ማስወጣት፣ የዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት…

Read More

በዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ የተመራው ቡድን በቤሮ ወረዳ የሩዝ ምርት ምልከታ አድርጓል።

በምዕራብ ኦሞ ዞን በቤሮ ወረዳ በሲያሊ ቀበሌ በመኸር ሰብል የተከናወኑ ተግባራትን ከ470 ሄክታር ባለይ ሩዝ ስራዎችን የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ ጨምሮ የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ጉብኝት አድርጓል።

Read More

በክልሉ የሞዴል አርሶአደሮች የመስክ በዓል ተከበረ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በክልሉ ግብርና ቢሮና በደቡብ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ማዕከል አዘጋጅነት በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ገሊት ቀበሌ የሞዴል አርሶአደሮች የመስክ ቀን ተከብሮ ውሏል። በበዓሉም በዞኑ ደቡብ ቤንች ወረዳ ጌሊት ቀበሌ በሞዴል አርሶአደሮች የለማው የበልግ የበቆሎ ምርት በክልል ከፍተኛ አመራሮችና በፕሮግራሙ ከሚደግፉ ወረዳዎች በተገኙበት ባለሙያዎች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል። በጉብኝቱ በ “አልካብ” ክላስተር…

Read More

በካርታ የተደገፈ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለአርሶአደሮች ተሰጠ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም በካፋ ዞን የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ምዝገባ ማረጋገጫ ደብተር ሰጠ። በዞኑ ጨና ወረዳ ቦባ ቆጫ ቀበሌ በፕሮግራሙ በሁለተኛ ዙር በካርታ የተደገፈ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ለ389 ባለ ይዞታዎች ዛሬ ተሰጥቷል። በመርሃግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተጠናቀቀው…

Read More

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት ተችሏል–የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በፍርድ ቤት ክርክር ከተደረገባቸው የወንጀል መዛግብቶች ውስጥ 3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት መቻሉን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል በርካታ የሪፎርም ስራዎች ተከናውነዋል።…

Read More