ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ነገ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Read More

በክልሉ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ የግብርና ልማት እንቅስቃሴን ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሻገር ከባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን የግብርና ቢሮ አስታወቀ ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ልማት አጋር አካላት ግንኙነት አማካሪ ካውንስል የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተደረገ ነው። በምክክር መድረኩ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የግብርና ልማት ዕድገትን በማፋጠን የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገቡ ያሉ ስኬታማ ተግባራትን ለማጠናከር የምርታማነት ዕድገት ማነቆ የሆኑ መሠረታዊ ችግሮችን ለይቶ እየፈቱ መሄድ ይገባል ብለዋል።…

Read More

የጥናትና ምርምር ሥራዎች በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለጸ

ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ ዓመታዊ የምርምር ጉባኤ “በጥናት የተደገፈ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ” በሚል ጭብጥ እያካሄደ ነው። በጉባኤው በተለያዩ ትምህርት እና ማህበረሰብ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ 30 የምርምር ውጤቶች እንደሚቀርቡ ማወቅ ተችሏል። ጉባኤውን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዱባሌ ሳህሌ:-የጋራ ጥረታችንን ወደፊት የሚያሻግረውን የኢኖቬሽን፣ የትብብርና ትስስር ጉባኤ በማዘጋጀታችን በኮሌጁ ማህበረሰብ ስም ኩራት ይሰማኛል…

Read More

ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት አግኝታለች

ኢትዮጵያ እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል። ባለስልጣኑ ሕገ-ወጥ የቡና ንግድን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከፌዴራልና ከክልሎች የፀጥታ፣ ከግብርናና ንግድ ዘርፎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ የቡና ምርትን ከማሳደግ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ በመሆኑ ውጤት…

Read More

መንግስት ለዜጎች ምቹና ተስማሚ አካባቢ ለመፍጠር እና የዜጎችን ህይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል:-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦንጋ ከተማ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንዳሉት፣መንግስት ለዜጎች ምቹና ተስማሚ አካባቢ ለመፍጠር እና የዜጎችን ህይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ክልሉ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና እንክብካቤ እንደሚታወቅ ጠቅሰው አሁን በ”ጽዱ…

Read More

የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ከጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ጎን ለጎን አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አከናወኑ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦንጋ ከተማ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛው ዙር ክልል አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዘመቻ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የኢፌደሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሚ በጋራ በመሆን አስጀምረዋል። የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ”ከጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ጎን ጎን በቦንጋ ከተማ…

Read More

“ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ሃሳብ ሁለተኛው ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዘመቻ ተጀመረ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦንጋ ከተማ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዘመቻ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የኢፌዲሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሚ በጋራ በመሆን ነው ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ባደረጉት ንግግር የአካባቢያችን…

Read More