July 2025
የ2018 በጀት ዓመት የደረጃ ‘ሐ’፣’ለ’ እና ‘ሀ’ ግብር ከፋዮች የግብር ማስጀመሪያ ክልላዊ ንቅናቄ እየተካሄደ ነዉ
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ) በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የደረጃ ‘ሐ’፣’ለ’ እና ‘ሀ’ ግብር ከፋዮች የግብር ማስጀመሪያ ክልላዊ ንቅናቄ መድረክ በሚዛን አማን ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ክልላዊ የንቅናቄ መድረኩ ”ለክልላችን ልማት ግብርን በታማኝነት በሚል መርሕ ቃል ነዉ እየተካሄደ የሚገኘዉ። በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ…
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ
“ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ያስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው፤ በስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት፣ በወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል ሊገለፅ የሚችል ነው። ሁለተኛው ለግሉ ዘርፍ የስራ አካባቢው ምቹ አልነበረም። ሶስተኛው ምርታማነት ነው። በግብርናም በኢንዱስትሪም ምርታማነታችን ውስን ነበር። ይህም በርካታ ተግዳሮቶች እነዲስተናገዱ አድርጓል። አራተኛው ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሁኔታን አልፈጠርንም። እነዚህን ጉዳዮች ጨክነን በመፍታት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱን መፍታት…
የመንግስትን የ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀንም በተመለከተ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከሰጡት ማብራሪያ :-
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ይህ ዓመት የኢትዮጵያ ማንሰራራት እንደሚሆን መናገሬ ይቃወሳል ። የለውጥ ማፅናት ተጠናቆ የሪፎርሙን ውጤት ማየት የቻልንበት ዓመት ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ታይተው ያልታወቁ ታላላቅ ድሎችን የተጎናፀፍንበት ዘመን ነው፡፡ የፓርላማ አባላት ክትትል እና ድጋፍን በማጠናከር ላደረጉት ጉልህ ተሳትፎ ምስጋና ይገባቸዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ጥያቄዎች
ፍትሃዊ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የዘመናት የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ፣ ህጋዊና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ የተጀመረው ሂደት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ጎረቤቶቻችንና አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን የባሕር በር ጥያቄውን ፍትሃዊነት እንዲረዱትና እንዲያግዙን፣ ወዳጅ ሀገራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ምን እየተሰራ ነው? መንግስት ደሀ ተኮር ሪፎርም አራማጅ ነኝ እያለ የመንግስት ሰራተኛውንና ዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ጥያቄዎች እንደቀጠሉ ናቸው
👉 የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና ከተፈጠረባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የመንግስት ሰራተኛው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ በዚህ ምክንያት የጤና ባለሙያዎች፣መምህራንና በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ፡፡ የመንግስት ሰራተኛን የኑሮን ደራጃን ከማሻሻል አኳያ በመንግስት ምላሽ ዙሪያ ምላሽ ቢሰጥበት? 👉 መንግስት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይሁን…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
sacsd
“ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ” በሚል መርህ ቃል ክልል ዓቀፍ የብክለት መግቻ ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። በንቅናቄው ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶር) እንዳሉት፣የአረንጓዴ አሻራ፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የአካባቢ ብክለት መግቻ የንቅናቄ ተግባራትን ከዘመቻ ባለፈ ተቋማት የየራሳቸውን ዕቅድ ይዘው በተቀናጀ መልኩ መመራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የተጀመሩ የገጠርና የከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የሌማት ትሩፋት ስራዎች፣ በፅዱ ኢትዮጵያ…
የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ኑሮ የሚቀይሩ እና ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ የሚያረጋግጡ ዜጋ ተኮር ሥራዎች በመሆናቸው ተጠናክሮ ይቀጥላሉ፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ”በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ 4! በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ክልላዊ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት ዓመታት ጀምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ኑሮ የሚቀይሩ እና ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ የሚያረጋግጡ ዜጋ…
