ግብርና ቢዚህ ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንዲያመጣ ነው የታቀደው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋልታ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የወጪ ንግድ ገቢያችን ዋልታም ነው ብለዋል። በርካታ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚሳተፍበት ዘርፍ በመሆኑ ትልቅ ስፍራ እንዲሰጠው መደረጉን ጠቁመዋል። ይህም በመሆኑ ግብርና ቢዚህ ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንዲያመጣ መታቀዱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የግብርናው ዘርፍ ከሌሎች ዘርፎች ልዩ ትኩረት ያገኘው ኢትዮጵያ…
