




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳይ ቢሮ በምዕራብ ኦሞ ዞን ከሀዱባ እስከ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የ46 ኪ.ሜትር የመንገድ ከፈታ ስራ ተጠናቆ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ርክብክብ ተደረገ ።
በርክብክብ መርሃግብር ላይ የተገኙት የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕራግ የመሠረተ ልማት አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዎ ሳፒ የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው በመኤኒት ሻሻ ወረዳ ሀዱባ ቀበሌን ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ጋር የሚያገናኝ የመንገድ ከፈታ ስራ የህዝቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል።
መንገዱ መከፈት የምዕራብ ኦሞ ዞንን ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከርና በአርብቶ አደሩ አካባቢ የግብይት ሰንሰለትን ከማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል።
የክልሉ መንግስት በዞኑ ውስጥ የህዝቡ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ እንደሚገኙ አንስተው ይህ ዛሬ ርክብክብ የተደረገው መንገድ የዞንና የወረዳ መንግሥት በቀጣይ መንገዱን የተሻለ ለማድረግ ተጨማሪ ተግባራትን በጋራ መከናወን እንደሚጠበቅባቸውና ህብረተሰቡ የእንክብካቤ ስራ እንዲያጠናክር አስገንዝበዋል።
የክልሉ አርብቶ አደር ቆላማ አካባቢዎች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ቦኒ በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት በአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ አካባቢ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎችን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የመንገድ ስራው የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳይ ቢሮ በ11 ሚሊዮን ብር በሆነ የገንዘብ ወጪ በማድረግ በመኤኒት ሻሻ ወረዳ ሀዱባ ቀበሌን ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ጋር የሚያገናኝ የ46 ኪ.ሜትር የመንገድ ከፈታ ስራ ነው ብለዋል።
የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ጌታቸው ኬኒ ይህ ዛሬ ርክብክብ የተደረገው የሀዱባ እስከ ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3መንገድ መከፈታ በአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ አካባቢዎች በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች ያሉት መሆኑን ተናግረዋል።
ከሀዱባ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ያለውን የመንገዱን ከፈታ ስራ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ርሰው ያስረከቡት ሀይሌ ገብሬ ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ አስተባባሪ ኢ/ር ሀይሌ ገብሬ ገልፀዋል።
ለመንገዱ ከፈታና ለስራው ስኬት አስፈላጊውን ሁሉ ላደረጉት የአካባቢው ነዋሪዎች እገዛና ትብብር ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
