የቤንች ብሔር የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ ቢስት ባር በሲዝ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች መከበር ጀምሯል።
ከቢስት ባር ሁነቶች መካከል አንዱ የሆነው የፖሊስ ማርሽ ባንድ የአደባባይ ትዕይንት አካሂደዋል።
የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” ለማክበረ የተለያዩ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብሔረሰቡ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች መከበር መጀመሩን የቤንች ሸኮ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።