Trendings

የትምህርት ሥርዓቱን የምናሻሽለው ኢትዮጵያን ከድህነት የሚያወጣ ትውልድ ለመፍጠር ነው- ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

Spread the love

የትምህርት ሥርዓቱን የምናሻሽለው ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣና ኢኮኖሚውን የሚሸከም ትውልድ ለመፍጠር ነው ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች የሚኒስቴሩን የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር)÷በትምህርት ሥርዓቱ ሪፎርም ማካሄድ ያስፈለገው ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣና ኢኮኖሚውን የሚሸከም ትውልድ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ መስዋዕትነት መክፈል እንደሚገባ የገለፁት ሚኒስትሩ በተለያዩ ዘርፎች እየተካሄዱ ላሉ ሀገራዊ የለውጥ ርምጃዎችም ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።

በዚህ ዘመን ከዓለም ጋር እኩል መራመድ አለመቻላችን እንደ ዜጋ ቁጭት ሊሰማንና ለለውጥ መትጋት ይኖርብናል ማለታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በትምህርት ሴክተሩም ይሁን እንደ ሀገር እየተተገበሩ ያሉ ሪፎርሞች በትክክልና በፍትሃዊነት ተግባራዊ እንዲደረጉ በማድረግ ለነገው ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ ይኖርብናልም ማለታቸዉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *