Edigetu Bezabhi

በክልሉ የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው:- አቶ ማስረሻ በላቸው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የዘር ብዝዬት ስራን በኮንታ ዞን በይፋ አስጀምረዋል። ድርጅቱ በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ በቡላ ሀማኮ ቀበሌ በ10 ሄክታር ማሳ የማሾና የቦለቄ መስራች ዘር በማባዛት ነው ስራውን የጀመረው። ድርጅቱ በክልሉ የመስተዳድር ምክር ቤት…

Read More

በኮንታ ዞን በአልሚ ባለሀብቶች እየለማ የሚገኘው የግብርና ስራ ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉ አቶ ማስረሻ በላቸው ተናገሩ።

በኮንታ ዞን በግል ባለሀብት እየለማ የሚገኘውን የግብርና ስራዎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ምልከታ አድርገዋል ። በኮንታ ዞን በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ኦሽካ ዴንቻ ቀበሌ በግል ባለሀብቱ እየለማ የሚገኘው የግብርና ልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትለል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ተናግረዋል ። የአቶ ግርማ እሸቴ የቡና ልማት እና የፍራፍሬ…

Read More

በክልሉ ሠላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ የፀጥታ መዋቅሮች ተቀናጅተው በሰሩት ስራ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ተመዝግቧል:-ኮሚሽነር ሰብሰቤ ሻዎኖ

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የ2015 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀምና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በታርጫ ከተማ እየመከረ ይገኛል ። በመድረኩ ኮሚሽነር ሰብሰቤ ሻዎኖ እንደተናገሩት በ2015 በጀት ዓመት በክልሉ በምዕራብ ኦሞ ዞን በሱሪ ፣ በቤሮና በጎርጌሻ ወረዳዎች፣በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ፣ በደቡብ ቤንችና በሸኮ ወረዳዎች የነበሩ የፀጥታ ችግሮችን ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰራው ስራ ውጤቶች ተመዝግቧል ብለዋል።…

Read More

ባንኩ ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ። የባንኩ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የአብሥራ ከበደ÷ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ ባንኩ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በእውቀትና ክህሎት የሚመሩ ጠንካራ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ ተከታታይ ሥልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ገልጸው፤…

Read More

እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!

ውድ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች! እንኳን ለየነቢዩ መሐመድ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መውሊደል ነቢ በሚከበርበት እለት፣ ሙስሊሞች መስጂድ ሄደው፣ በጋራ፣ ጸሎት ያድርጋሉ፡፡ የታላቁን ነቢይ ስራዎች፣ አስተምህሮቶች ይዘክራሉ፡፡ ነቢዩ በህይወት ሳሉ የነበራቸውን፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ይቅር ባይነት ያስታውሳሉ፡፡ ከመስጂድ ከወጡም በኋላ፣ ያላቸውን ከሌላቸው ጋር በመካፈል፣ ለወገኖቻቸው ሁሉ ትሁት በመሆን፣ የበደላቸውን ይቅር በማለት፣ እንደ ዲናቸው መሪ፣ ትህትናን፣ ደግነትን እና ይቅር…

Read More

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሚያስተዳድራቸው የልማት ድርጅቶች ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገቡ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሚያስተዳድራቸው የልማት ድርጅቶች በ2015 ዓ.ም ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገባቸውን ይፋ አደረገ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ያስሚን ወሀብረቢ፤ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ በ2015 ዓ.ም የሚያስተዳድራቸው የልማት ድርጅቶች የነበራቸውን የስራ እንቅስቃሴ አብራርተዋል። ከሀገራዊ ለውጡ በፊት አብዛኛዎቹ የልማት ድርጅቶች በዕዳ የተዘፈቁ፣ ከኪሳራ ያልተላቀቁና የፋይናንስ አስተዳደራቸውም በውስብስብ ችግር ውስጥ እንደነበሩ አስታውሰዋል።…

Read More

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለግብርናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኩ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡ በውይይቱ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች በመስኖ ስንዴ ልማት፣ በእንስሳት ልማት፣ በሌማት ትሩፋት ፕሮግራም እና በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተከናወኑ ተግበራትን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል።…

Read More

በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ

በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና መጠናቀቁን ፓርቲው አስታወቀ። ከመስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል። በማጠቃለያ መድረኩም የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስልጠናውን ማጠቃለያ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት የስራ ስምሪት ሰጥተዋል። ስልጠናው ወሳኝ በሆኑ ሃገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም…

Read More

በመኸር ወቅት 513 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት እየተሠራ ነው

በመኸር ወቅት 17 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታር በማልማት 513 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ፣ ትግራይ፣ ሐረሪ ክልሎች እና በድሬዳዋ አስተዳደር 17 ሚሊየን 390 ሺህ 818 ሔክታር ለማረስ መታቀዱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡ እስካሁንም 14 ሚሊየን 137 ሺህ 156 ሄክታር በባሕላዊ…

Read More

የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ (የቤኔ ሻዴዬ ባሮ) በቦንጌ ሻንበቶ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

የካፈቾ ብሔር የጥንት ታሪክና የዳበረ ባህል ባለቤት ነው። ከዘመን ዘመን ተሻግሮ ለዚህ ትውልድ የደረሱ የተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች አሏቸው። ከነዚህም አንዱ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ በቦንጌ ሻንበቶ እየተከበረ ያለው የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ “የቤኔ ሻዴዬ ባሮ”በዓል ነው። የቤኔ ሻዴዬ ባሮ በካፈቾዎች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የብሔሩ ታላቅ ዕሴትና የማይዳሰስ ቅርስ ነው። የካፋ ህዝብ ዘመን አቆጣጠር የአዝመራ ወቅትን…

Read More