አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ውጥረታቸውን ለማርገብ በለንደን እየመከሩ ነው
የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት በሁለቱ ልዕለ-ኃያላን ሀገራት መካከል የተፈጠረውን የንግድ ውጥረት ለማርገብ ዛሬ በእንግሊዝ ለንደን ለውይይት ተቀምጠዋል። በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን የንግድ ውጥረት ለማርገብ ባለፈው ወር በስዊዘርላንድ፣ ጄኔቫ ከተማ ሁለቱም ወገኖች አብዛኛውን ታሪፍ እንዲያነሱ ያስቻለ ቅድመ-ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ በአገራት ላይ ሊጥሉት ያቀዱትን ታሪፍ ለ90 ቀናት እንዲዘገይ ካሳወቁ በኋላ በአንጻሩ በቻይና…
