አመራሩ የንቅናቄው አጀንዳዎች ፋይዳን በመገንዘብ በላቀ ዝግጁነት መፈጸም ይገባል። አቶ ፍቅሬ አማን
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት እየተከናወኑ ያሉ የንቅናቄ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት በአመያ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፥ በየደረጃው ያለው አመራር የንቅናቄው አጀንዳዎች ፋይዳን በተገቢው በመገንዘብ በላቀ ዝግጁነት መፈጸም እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል። ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውና ሀገራዊ ፋይዳቸው የላቁ አጀንዳዎች በክልሉ የብልጽግና…
