የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማፋጠን የሴቶችን ተሳትፎ የበለጠ ማሳደግ ይገባል – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማፋጠን የሴቶችን ተሳትፎ የበለጠ ማሳደግ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለፁ። 6ኛው የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒትና ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በንግድ ትርዒቱ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፣ አፍሪካ በ2063 ለማሳካት ከያዘቻቸው አጀንዳዎች አንዱ የሴቶችን እኩልነትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት…
