




የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ በክልሉ በሁሉም መስክ ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጢ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ለዚህም የብልጽግና ፓርቲ አባላት ጤናማና ለፓርቲው ግንባር ቀደም በመሆን ፊት ወጥተው በሀሳብ ላይ ትግል ማድረግ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል ።
በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮችና የብልጽግና ህብረት አባላት በቀረበው የመወያያ ሰነድ መነሻ በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በአፍራሽ አካላት ዘንድ የሚስተዋሉ ለሀገር የማይጠቅሙ ከፋፋይ አጀንዳዎችን በጋራ መታገል ይገባል ብለዋል።
ፓርቲውን ለማሻገር በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ ህዝቡን የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ኑሮ ውድነትን ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን በመፈተሽ የፓርቲውን ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ቦኒ አመራሩ እና አባላቱ አሁን በሀገራችን ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታን በመገንዘብ ለዚህም የሚመጥን ተግባር በመስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የፓርቲዉ አባላትና አመራሩ ሚናውን በተገቢው በመወጣት የአፍራሽ ሀይሎችን ተልዕኮ መታገል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
መድረኩ በቀረበው ሰነድ ላይ የብልጽግና ህብረት አባላት አስተያየት እና ከመድረኩ ማጠቃለያ ሀሳብና አቅጣጫ ተሰጥቶ ተጠናቋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
