

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በፓርቲ መሪነትጨበዘላቂነት ለመፍታት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቦንጋ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ባደረጉት በመክፈቻ ንግግር ባለፉት ወራት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በህዝቡ የተነሱ አግባብነት ያላቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት በየደረጃዉ የሚገኝ የመንግስት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ህዝቡን ባሳተፈ መንገድ የመልካም አስተዳደር የመፍቻ እቅድ በማዘጋጀት ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል።
የህዝቡን የሠላም እና የልማት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትና ሁሉ አቀፍ መልካም አስተዳደር ማስፈን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው የደረጃዉ ባሉ በግብርና፣በጤና እና ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተደረገውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ግምገማ አፈጻጸም ሪፖርት ማዕከል ያደረገውን ውይይት አስጀምረዋል፡፡
የህዝቡን መሠረታዊ ችግሮችን መፍታት፣ አገልግሎት ዕርካታን ለማረጋገጥ ጊዜው ይጠይቃል ያሉት አቶ ፍቅሬ በቀጣይ በየማህበራዊ መሠረቱ በተደረጉ ውይይቶች የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
በክልሉ በቀጣይ 90 በፓርቲና በመንግስት የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጎ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ተመላክተዋል።
