Trendings

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብር ከፋዮች የ2016 ግብራቸውን በቴሌ ብር አማካኝነት እንዲከፍሉ አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ ተመቻችቷል- የክልሉ ገቢዎች ቢሮ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የገቢዎች ቢሮ የደንበኞች አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዘርፍ ኃላፊና የቢሮው ምክትል ኃላፊ ቢሮው የክልሉን ገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለማዘመን በተለይ በኢ-ታክስ /በኤሌክትሮኒክስ የታክስ ስርዓት/ በመዘርጋት ታክስን ለመሰብሰብ እንዲቻል ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር የክልሉ ግብር ከፋዮች በቴሌ ብር አመታዊ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ሲሰራ የነበረው ስራ መሳካቱን ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የክልሉ የታክስ አስተዳደርና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ዘመኑ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ ስርዓት ጋር በማስተሳሰር ክልሉ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚ ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ ለክልሉ ህዝቦች ሁሉን አቀፍ ልማት የሚውለውን የፋይናንስ ወረት ለመሰብሰብ የኢ-ታክስ ስርዓቱ በክልሉ መዘርጋቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አቶ ወንዱ ታደሰ አብራርተዋል፡፡

ይህ የኢ-ታክስ /የኤልክትሮኒክስ ታክስ ስርዓት/ አገልግሎት በቴሌ ብር አማካኝነት መዘርጋቱ ግብር ከፋዩን በመመላለስ የሚያጠፋውን ግዜና እንግልት የሚያስቀር ፍትሃዊና ቀልጣፋ የሆነ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት የምንገነባበት በመሆኑ ግብር ከፋዩ በአቅራቢያው በሚገኝ የቴሌ አገልግሎት ማዕከል በመቅረብ የነጋዴ ቴሌ ብር አካውንት በመክፈት የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

ከሐምሌ 01/2016 ጀምሮ በ28 የታክስ ማዕከላት የሚገኙ 32,725ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን በቴሌ ብር ይከፋላሉ ያሉት አቶ ወንዱ ታደሰ የክልላችን ግብር ከፋዮች ይህንን ምቹ እድል በመጠቀም ግብርን በወቅት በመክፈል ፣ ራስን ከቅጣት ነጻ በማድረግ ከወቅቱ ጋር በመዘመን ጊዜን ለተሻለ ምርት እና አገልግሎት ግብር ከፋዮቻችን መጠቀም እንዲችሉ አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *