የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፎረም በደቡብ ኮሪያ ተካሄደ
ከ200 በላይ የሚሆኑ የኩባንያ ባለቤቶች በተገኙበት የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት እድል ለኢንቨስተሮች የሚያስተዋውቅ ፎረም በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ተካሂዷል፡፡ በዝግጅቱ ላይ በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የተሻለ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ማበረታቻዎች እንዳላት አስገንዝበዋል፡፡ በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር ለመፍጠር በመንግስት የተደረጉ ፖሊሲ ማሻሻያችን፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች እና ምቹ የንግድ…
