በግንባታ ላይ የሚገኙ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀዉ ለአገልግሎት እንዲበቁ እየተሰራ ነው፦ኢንጂነር በየነ በላቸው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ወራት 61 የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ከ64ሺ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ የክልሉ ውሃ፣ ማዕድና ኢነርጂ ቢሮ ገለጸ። የክልሉ ውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው የተመራ ልዑክ በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ በግዝመሬት እና ሺሚ ቀበሌዎች በግንባታ ላይ የሚገኘው የንጹህ…
