በክልሉ የሚከናወኑ የፌደራል መንገድ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎች ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ
የኢፌዲሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጋር በመተባበር አዲስ ተሻሽለው በወጣው ካሳ አዋጅ ላይ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ነዉ። የስልጠናዉን መድረክ የከፈቱት በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሀገራዊ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ሥራአስፈጻሚ አቶ ተዎድሮስ ተገኝ እንዳሉት፣ መድረኩ አዲስ በተሻሽለው የካሳ አዋጅ፣ በክልሉ ለሚከናወኑ የፌዴራል መንገድ…
