የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በጭዳ ከተማ የአቅሜ ደካማ መኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመረ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኮንታ ዞን በምትገኘው ጭዳ ከተማ፣ አቅመ ደካማና ጠያቂ ለሌላቸው እናት የመኖሪያ ቤት ግንባታ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ። ይህ የክረምት ወራት የበጎ አድራጎት ሥራ የክልሉ መንግሥት አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ የያዘው ሰፊ መርኃ ግብር አካል መሆኑ ተገልጿል። የቤቱ ግንባታ የተጀመረላቸው ወ/ሮ በየነች መኮንን፣ በከተማው ውስጥ በችግርና ያለረዳት በደሳሳ…
