አቶ አደም ፋራህ በአዳማ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ጎበኙ
በምክትል ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በአዳማ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ጎበኙ። አቶ አደም ፋራህ፣ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዳማ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተናበበና በተቀናጀ መልኩ በአንድ ማዕከል ለመስጠት የተቋቋመውና “ጋዲሳ ኦዳ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን…
