በክልሉ ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ ነው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 8 ሺህ 4መቶ 19 ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። እየተሰጠ የሚገኘው የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደሆነም ተገልጿል። የቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ደስታ ገነመ እንዳሉት፥በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ከሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች መካከል የተማሪዎች…
