ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብር፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ትሥሥር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል
