ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው፡ – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥራ የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ዘገባ ለመስራት ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ለ37ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አስታውሰዋል፡፡…
