አስፈጻሚ ተቋማት የዞኑን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በሚያስችሉ ተግባራት ላይ እንዲያተኩሩ ተጠየቀ።

የሸካ ዞን ምክርቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ በስሩ የሚከታተላቸዉን የአስፈጻሚ አካላት የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ገምግሟል ። መድረኩን የመሩት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በወቅቱ እንደገለጹት በግማሽ ዓመቱ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም በህብረሰቡ ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ዋና አስተዳዳሪው ከግብዓት ገንዘብ አሰባሰብ ጋር…

Read More

87ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ተከበረ::

87ኛው የየካቲት 12 መታሰቢያ በአዲስ አበባ ሥድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት ተከብሯል፡፡ ዕለቱ የአዲስ አበበ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የታሰበው፡፡ 6 ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልትም ከንቲባ አዳነች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ከንቲባዋ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ የዛሬዋን መልክ የያዘችው በአባቶቻችንና በእናቶቻችን ውድ መስዋዕትነት ነው ብለዋል። ለነፃነታችንና ለሰላማችን…

Read More

በአፍሪካ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊና አካታች የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት አህጉራዊ ልማትና እድገት ማፋጠን ይገባል::

በአፍሪካ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊና አካታች የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት አህጉራዊ ልማትና እድገትን ማፋጠን እንደሚገባ በትምህርትና ልማት ዘርፍ የሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት ገለጹ። 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ሥርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት” በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል። የሕብረቱ ጉባዔ መሪ ሃሳቡን ትምህርት…

Read More

በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ምን ምን ስራዎች እየተከናወኑ ነው” የአፈር አስዳማነት ችግር እንዴት ሊፈታ ይችላል?

በሀገራችን ኢትዮጵያ የግብርና ምርትና ምርታማነት በመጨመር የግብርና ክፍሌ ኢኮኖሚ ለማሳደግ ሰፊ ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የግብርናውን ዘርፍ ውጤታማነትና ምርታማነት በምርምር የተረጋገጡና የተደገፉ ለማድረግ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ዋነኛውና አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ክልላችን ሲደራጅ ያለውን አቅም ለይቶ በማወቅ በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን የመልማት ፍላጎት ለማሟላት የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ ግብ ጥሎ ወደ ስራ ተገብቷል። ከዚህም መነሻ በክልሉ ያለውን እምቅ…

Read More

ሴቶችን ማስተማር መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ ሚና አለው -ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ::

ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በተጨማሪ መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ ሚና አለው ሲሉ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተናገሩ፡፡ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ” እሷን አስተምሩ እና አፍሪካን ለውጡ” በሚል መሪ ቃል በ28ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ድርጅት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸው ÷ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በተጨማሪ…

Read More

ሰልጣኝ አብራሪዎች የኢትዮጵያን አየር ኃይል የስኬት ጉዞ የሚያስቀጥሉ ተረካቢ ትውልድ ናቸው – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ::

ሰልጣኝ አብራሪዎች የኢትዮጵያን አየር ኃይል የድልና የስኬት ጉዞን የሚያስቀጥሉ ተረካቢ ትውልድ መሆናቸውን በመገንዘብ ሙያዊ አቅማቸውን ለማሳደግ እና በቴክኖሎጂ ራሳቸውን ለማብቃት ይበልጥ መዘጋጀት አለባቸው ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ። ዋና አዛዡ በ L-39 እና በሴሲና 172 ስኳድሮኖች የሶሎ በረራን ስልጠና በሚገባ አጠናቀው ወደ ቀጣዩ ምዕረፍ የተሸጋገሩ ሰልጣኝ አብራሪዎችን በአየር ኃይል…

Read More

በአፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ጽንፈኝነት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጥ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል::

በአፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ጽንፈኝነት፣ ግጭት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጥና ሌሎችም የጸጥታ ሥጋቶች የአህጉሪቷ ፈተና ሆነው በመቀጠላቸው ዘላቂ መፍትሄ ሊበጅላቸው እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ገለጸ። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሠላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ፤ ከ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የአህጉሪቱን የጸጥታ ጉዳዮች አስመልክተው ማምሻውን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፣ በአፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ጽንፈኝነት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣…

Read More

የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑ ተመላከተ::

37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። ጉባኤውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ፥ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የእንግዶች ቆይታ ያማረ እንዲሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በሶማሊያ መንግስት በኩል የቀረበው ውንጀላ ኢትዮጵያ ለእንግዶች ያደረገችውን እንክብካቤ የማይመጥን ነው ብለዋል። ሁሉም መሪዎች ያለ ልዩነት አቀባበልና መስተንግዶ እንደተደረገላቸውም ጠቁመው፥…

Read More

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ::

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎች በማሳለፍ ዛሬ ማለዳ ተጠናቋል። ጉባኤው “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ ሕብረቱ ባዘጋጀው የ2024 መሪ ሀሳብ ከቅዳሜ ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። በጉባኤው የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሕብረቱ ተቋማትና አደረጃጀቶች አመራሮች ተሳትፈዋል።…

Read More

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው::

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሂደት በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ገለጸ፡፡ የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳለ አሰፋ÷ በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡ ከነዚህ መካከል በ926 ሚሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ የሚገኘው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ አንዱ መሆኑን ተናግረው፤ የግንባታ ሒደቱ 54 በመቶ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች…

Read More