በዋና ዋና ማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች የተመዘገበው አፈጻጸም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7 ነጥብ 9 በመቶ እንደሚያድግ አመላካች መሆኑ ተገለፀ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል። በመድረኩም ያለፉት ስድስት ወራት የኢኮኖሚ ማህበራዊ እንዲሁም የፍትህና አስተዳደር ዘርፍ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፤ የኢኮኖሚ ዘርፍ አፈጻጸምን ባቀረቡበት ውቅት ኢትዮጵያ በ2015 የ7 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ማስመዝገቧን አስታውሰዋል። በተያዘው በጀት…
