በምዕራብ ኦሞ ዞን በማጂ ቱም የስልጠና ማዕከል ”የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ 10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
ስልጠናው አመራሩን በአመለካከትና በተግባር አንድነት የሚገነባና የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም የሀገርን ሠላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ አቅም የፈጠረ እንደሆነ ተገልጿል። የምዕራብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በድሉ መዓዛ በማጠቃለያቸው፦ ስልጠናው አመራሮች ያሉበትን ቁመና እያመላከተ የዕውቀት አድማሳቸውን በማሳደግ ረገድ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል። የተሻለ መሪ ለመሆን አመራሮች በሥነ-ምግባር እራሳቸውን ማነጽ እንደሚገባቸው የጠቀሱት አቶ በድሉ በተለይም ዕውቀታቸውን…
