ኢትዮጵያ አንድነት የሚገለጥባት ድንቅ ምድር ናት – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ኢትዮጵያ አንድነት የሚገለጥባት ድንቅ ምድር መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ህብር የሀገሪቱን አንድነት እንደማይሸረሽረው ፤ ሀገራዊ አንድነቱም የኢትዮጵያን ህብራዊነት እንደማይጠቀልለው አውስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ “ህብራዊነቷ ጌጧ፣ መልኳ፣ ጸጋዋ፣ ሐብቷ ነው ፤ አንድነቷ ደግሞ ኃይሏ፣ ጉልበቷ፣ ዐቅሟ…
