ሚዲያ የፈጠራት እና እውነተኛዋ ብርቱካን
ቤተሰብ የሠራት እውነተኛዋ ብርቱካን ባለትዳር፣ የቤት እመቤት ነች፤ መልካም የሚባል ትዳር ይዛም ከባንክ ሠራተኛው ከባለቤቷ ጋር አብሮ ይኖሩ እንደነበር በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ በኢቢኤስ ውስጥ የተፈጠረችው ብርቱካን ግን ከዚህ ተቃራኒ ነች፤ በጣም ብዙ ስቃይ ውስጥ ያለፈች፣ በርካታ ወንዶች ተፈራርቀው የደፈሯት እና ተደፍራ ለመውለድ የተገደደች፡፡ ቤተሰቦቿም አንዱን በስደት ሌላውን በሞት ተነጥቃ በሰው ቤት ተንከራትታ የተማረች ነች በፊልም የቀረበችው…
