የክልሉን የታክስ አስተዳደርና የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑን የገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ለ114 የገቢ ተቋም ባለሙያዎች በሲግታክስ የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየተሠጠ ነው። የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ታደሰ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው ቢሮው የታክስ አስተዳደርና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን የዘመነ ለማድግ ከዚህ ቀደም ብዙ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል። ባለፋት ጊዜያት በሲግታክስ ተጠቅመን የግብር ግመታንና ውሳኔውን ለማውጣት…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ዛሬ ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በዞን፣ በክልል እና ከተሞች ደረጃ ከተካሄዱ ውይይቶች የቀጠለ ውይይት ዛሬ በፌዴራል ደረጃ አካሂደናል። ይኽ መድረክ በየደረጃው የተሰበሰቡ የንግዱ ዘርፍ ጉዳዮች እና ሃሳቦች በሀገር አቀፍ እቅዶች እና የልማት ግቦች ዝግጅት ግብዓት ይሆኑ ዘንድ ለማካተት የተዘጋጀም ነው።

Read More

አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ውጥረታቸውን ለማርገብ በለንደን እየመከሩ ነው

የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት በሁለቱ ልዕለ-ኃያላን ሀገራት መካከል የተፈጠረውን የንግድ ውጥረት ለማርገብ ዛሬ በእንግሊዝ ለንደን ለውይይት ተቀምጠዋል። በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን የንግድ ውጥረት ለማርገብ ባለፈው ወር በስዊዘርላንድ፣ ጄኔቫ ከተማ ሁለቱም ወገኖች አብዛኛውን ታሪፍ እንዲያነሱ ያስቻለ ቅድመ-ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ በአገራት ላይ ሊጥሉት ያቀዱትን ታሪፍ ለ90 ቀናት እንዲዘገይ ካሳወቁ በኋላ በአንጻሩ በቻይና…

Read More

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለክልሎች የሚከፋፈለው የጋራ ገቢ የድጎማ በጀት እያደገ መጥቷል፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለክልሎች የሚከፋፈለው የጋራ ገቢ የድጎማ በጀት እያደገ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። በውስን ዓላማ የድጎማ በጀቶች ትልልፍ እና በጋራ ገቢዎች ክፍፍል በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ የዳሰሳ ጥናት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የሀብት ክፍፍል ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን የምክር ቤቱ አፈ ጉብኤ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥ…

Read More

በ2017/18 የመኸር ግብርና ስራዎች ከሚለማው ከ401 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ 17.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እንደሚሰራ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ

በመኸር የግብርና ስራዎች ከ126 ሺህ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያም ጥቅም ላይ እንደሚውል ታውቋል። አልቆ ማቀድ፣አልቆ መስራት ለምርታማነት ዕድገት! በሚል መሪ ቃል የግብርና መኸር ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተጀምሯል። በንቅናቄው መድረክ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታትም…

Read More

በቅርቡ የኢትዮጵያን ቱባ ባህል የሚያስተዋውቅ የባህል ቡድን ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ይጓዛል

የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ የሚገነቡ የኪነጥበብ ስራዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት የማቅረብ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል አሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ። ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት፤ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ከፍ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት በባህልና ኪነጥበብ ዘርፎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በዚህም የኢትዮጵያን ብዝሃ ባሕልና የጥበብ ስራዎችን በማስተዋወቅ ገጽታን የመገንባት ተግባራት በስፋት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ይህንንም ተከትሎ በተለይ በሰርከስ እና በስዕል ዘርፍ…

Read More

በሎስ አንጀለስ ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን ማሰር በመጀመሩ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብሔራዊ ዘባቸውን ወደ አካባቢው አዘመቱ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 2ሺህ የብሔራዊ ዘብ ጠባቂዎችን ወደ ሎስ አንጀለስ አሰማርተዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያደረጉት ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን የማሰር ዘመቻን ተከትሎ ለተነሳው ተቃውሞ ምላሽ ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ተቃውሞውን መቋቋም ተስኗቸዋል ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፥ የፌደራል መንግስት ችግሩን መፍታት ባለበት መንገድ ይፈታልም ብለዋል። የካሊፎርኒያ ስቴት ገዥ የሆኑት ጋቪን ኒውሶም የትራምፕ ርምጃ ውጥረቶችን እንደሚያባብስ ተናግረዋል። “ይህ የተሳሳተ ተልእኮ ነው…

Read More

በክልሉ ስፖርት ከመዝናኛነት ባለፈ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታው እየጎላ መምጣቱ ተጠቆመ ።

የአላየሁ መላኩ አትሌቲክስ ክለብ ሁለተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በማስመልከት የ5 ኪሎሜትር ህዝባዊ የጎዳና ላይ ሩጫ በገዋታ ወረዳተካሂዷል ። “አኩሪ አትሌቶችን በማፍራት የሀገራችንን ለውጥ እናረጋግጣለን ” በሚል መሪ ቃል በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ በሂንጊዶ ከተማ በተደረገው የጎዳና ላይ 5 ኪሎሜትር ሩጫ ከ300 በላይ ወንዶችና ሴቶች ተሳትፈዋል ። በመርሃግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?

ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ‘’የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?’’ በሚል አምድ ሥር አጠቃላይ የክልላችንን ገጽታ፣  የምዕራብ ኦሞ፣ የካፋ፣ የዳዉሮና የቤንች ሸኮ ዞኖችን አጠቃላይ ገጽታ የሚያሳዩ ጽሁፎችን እንደየቅደምተከተላቸው ለውድ አንባቢዎቻችን አድርሰናል፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ከክልላችን ዞኖች አንዱ የሆነውን የሸካ ዞንን እንቃኛለን፡፡ መልካም ንባብ! የሸካ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ውስጥ ከሚገኙ ስድስት …

Read More