በቦንጋ ከተማ በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ እየተገነባ ያለው ቤተ መጻሕፍት
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ እየተገነባ ያለውን ቤተ መጻሕፍት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡ ለግንባታው ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ እና ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ እንደሚሸፈን የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ የማታለም ቸኮል (ኢ/ር) ተናግረዋል፡፡ ግንባታው በጥራት እየተከናወነ መሆኑን…
