ከክልሉ ሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አመራሮች እና ባለሙያች እንዲሁም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ
ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል። የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን የመደመር ትውልድ የቤተ መጽሐፍት…
