ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ኤምባሲ የልዑካን ቡድን ጋር መከሩ ።
የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ መልዕክተኞች በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ድንበር አከባቢ የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ምክክር በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል የቆየውን ታሪካዊ ወዳጅነት በማስቀጠል የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነት እና ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማስቀጠል እንዳለበት በውይይቱ ተመላክቷል። ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ሪፑብሊክ ጋር ሰፊ ድንበር የሚጋራ በመኾኑ፥ በድንበር አከባቢ የሚከሰቱ ችግሮችን በዘላቂነት…
