መንግሥቴ የሚመሰገን ከሆነ በዕዳ አያያዝ በሠራው ሥራ መሆን አለበት፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን የዕዳ ጫና በመቀነስ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ገለጹ። ኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት በከባድ የዕዳ ጫና ውስጥ እንደነበረች ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተለይም ቀደም ሲል ይወሰድ የነበረው የንግድ ብድር ለሀገሪቱ ትልቅ ፈተና እንደነበር ጠቁመዋል። ይህ ዓይነቱ ብድር የሀገሪቱን የፋይናንስ አቅም በማዳከሙ፣ አበዳሪዎች ተጨማሪ ብድር ለመስጠት ተጠራጥረው እንደነበርም አብራርተዋል። የሌብነት መስፋፋት እና…
