ከሸማቂ ሃይሎች ጋር ውይይት አድርጎ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መሞከር አዲስ ነገር አይደለም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከሸማቂ ሃይሎች ጋር ውይይት አድርጎ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መሞከር አዲስ ነገር ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሀገራት የሚተገበር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም በዚሁ አግባብ ከሸኔ ጋር ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፤…
