በክልሉ በፌደራል መንግሥት የሚገነቡ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታዎች ላይ የሚታየዉ የአፈጻጸም ችግር ሊታረም እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ አሳሰቡ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከኢፌዲሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አዲስ በተሻሻለው የካሳ አዋጅ ቁጥር 1336/2016 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና በክልሉ በፌደራል መንግሥት የሚገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃና የክልሉን ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተዋል። አዲስ ተሻሽለው የወጣዉ የካሳ አዋጅ ንብረት የመገመት፣ የመክፈል እና የማስነሳት ስራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ…
