ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ በግብርናው ክፈለ-ኢኮኖሚ በርካታ ለዉጦች ተመዝግበዋል። አቶ ማስረሻ በላቸው
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ በግብርናው ክፈለ-ኢኮኖሚ በርካታ ለዉጦች መመዝገባቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የሰባት ዓመታት የለውጥ ጉዞና የተገኙ ትሩፋቶችን በሚመለከት በጽ/ቤታቸው ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግልጫ ሰጥተዋል። መጋቢት 24/2010 ዓ/ም የለውጡ መንግሥት ወደ መንበረ ስልጣን ሲመጣ፥ ሀገሪቱ ዘርፈብዙ ችግሮች ውስጥ እንደነበረች ያወሱት…
