የሻይ ልማት ከኢኮኖሚ ጠቃሜታው ባሻገር የአካባቢውን ስህነ ምዳር በመጠበቅ ረገድም ሚናው የጎላ ነው፦ አቶ ማስረሻ በላቸው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን በሻይ አመራረት ዘዴ ላይ ለዞን፣ ለወረዳና ለቀበሌ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል፡፡ የስልጠናውን መድረክ ያስጀመሩት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የሻይ ልማት በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ሂደት ውስጥ ለአካባቢያችን ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት አይናተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡…
