የካፈቾ ብሔር የአዲስ ዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ) እየተከበረ ይገኛል
የ2017 ዓ/ም የካፈቾ ብሔር የአዲስ ዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ) በዓል በደማቅ ህዝባዊ ተሳትፎ የነገስታት መናገሻ በሆነው ‹‹ቦንጌ ሻምበቶ›› በደማቅ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅበው እየተከበረ ይገኛል። የፌዴራል ፖሊሲ ማርች ባንድ ለዕለቱ ክብር እንግዶች ደማቅ አቀባበል አድርገዋል። በበዓሉ ለመታደም ከሀገረ ሩስያ የተገኙ የውጭ ሀገራት ዜጎች የሀገራቸውን ባህል የሚያሳይ የባህል አልባሳትን በመልበስ በበዓሉ ታድመዋል። የካፈቾ ባህላዊ ምክር ቤት (ምክሬቾ) አባላት…
