በፖሊቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረጉ ወይይቶች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ አጋዥ በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በሸካ ዞን የሚገኙ የተለያዩ ተፎካካሪ ፖሊቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተናገሩ
ሸካ ዞን የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ሰባተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጌጫ ከተማ ምክክር አካሂዷል ። የሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሚና የላቀ መሆኑም በመድረኩ ተጠቅሷል ። የምርጫው አተገባበርና የህግ የበላይነትን በማክበር በፖሊቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደርግ ፉክክር ሚዛኑን መጠበቅ እንዳለበትም የተገለጸ ስሆን ለህግ ተገዢ መሆን በሀገር ግንባታና በዴሞክራሲ ምህዳር መስፋት…
