የኢትዮጵያ እና የተመድ የ80 ዓመታት ታሪካዊ ቁርኝት
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስምንት ዐሥርተ ዓመታት ጉዞ ውስጥ፣ ኢትዮጵያ በጋራ ደኅንነት፣ በሰላም እና በልማት ፅኑ አቋም ይዛ በዓለም አቀፍ መድረክ ደማቅ አሻራዋን አኑራለች። ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሻገረው የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ጉዞ ተመድ የተመሠረተበትን በዓል ሲያከብር፣ የድርጅቱ ቀዳሚ መሥራች እና ንቁ ተሳታፊ የሆነችው ሀገራችን በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፣ በሰላም ማስከበር እና በልማት ትብብር ረገድ ያሳለፈቻቸው…
