የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ የህዝብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት አባላት በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮርደር ልማት እና የመሰቦ አንድ ማዕከልን ጎብኝተዋል። የልማት ፕሮጀክቶችን በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት ፤ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። እንደ አባላቱ ገለጻ፣ መሰል የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው የዴሞክራሲ ስርዓቱን በጽኑ…
