ለሀገራችን ልማትና ዕድገት የሚረዳ ተዓማኒነት ያለዉ መረጃ ለማደራጀት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሚና ከፍተኛ ነው፦ አቶ በላይ ተሰማ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የወሳኝ ኩነቶች ዘርፍ ከክልል ቢሮ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት የጋራ ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት፤የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እንደተናገሩት፤ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ እና አስተዳደራዊ ዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ…
