በ2017/18 የመኸር ግብርና ስራዎች ከሚለማው ከ401 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ 17.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እንደሚሰራ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ
በመኸር የግብርና ስራዎች ከ126 ሺህ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያም ጥቅም ላይ እንደሚውል ታውቋል። አልቆ ማቀድ፣አልቆ መስራት ለምርታማነት ዕድገት! በሚል መሪ ቃል የግብርና መኸር ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተጀምሯል። በንቅናቄው መድረክ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታትም…
