Trendings

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ለቦንጋ የመደመር ትውልድ ቤተ-መጻሕፍት ላይብራሪ የኮምፒውተር ድጋፍ አደረገ።

ኮርፖሬሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ለተገነባውን ቤተ-መጻሕፍት የዲጂታል ላይብራሪ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ዋጋ ግምት ያላቸዉን 20 ኮምፒዩተሮችን ድጋፍ አድርጓል። በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ኮርፖሬሽኑ የክልሉን ግብርና ለማዘመን የግብርና ግብዓት እና የሜካናይዜሽን አቅርቦት ለማሳለጥ ማዕከል…

Read More

በሌማት ትሩፋት ስራዎች የተለዩ 73 መንደሮችን ሞዴል አድርጎ ማሳካት የአመራሩ ቁልፍ ተልዕኮ መሆኑን አቶ ማስረሻ በላቸው አሳሰቡ ።

በክልሉ በሌማት ትሩፋት ስራዎች የተለዩ 73 መንደሮችን ሞዴል አድርጎ ማሳካት የአመራሩ ቁልፍ ተልዕኮ ሊሆን እንደሚገባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ተናግረዋል ። በክልሉ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትና የቀጣይ አቅጣጫን የሚያመላክት የመወያያ ሰነድ በግብርና ቢሮ ምክል ቢሮ ኃላፊና የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ታመነ በቀለ ቀርቧል። ተጠናክሮ በቀጠለው…

Read More

የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የምችል የምርት ሂደት ለተሻለ ገበያ አማራጭ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ በዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም የሚደገፉ ተፋሰሶችን ከግል የልማት ህብረቶች (SLMP/RLLP) ጋር በጋራ ለማልማት የአጋርነት ስምምነት መፍጠሪያ አውደ ጥናትና መግባቢያ ስምምነት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። ይህ ፕሮግራም በሀገር ደረጃ በርካታ ተሞክሮ የተቀመረበት ሲሆን በክልላችን በ3 ዞኖች፣በ6 ወረዳዎች እና በ55 ተፋሰሶች ላይ ከ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ 4 ዓመታት የሚተገበር…

Read More

ሙስናን መከላከል አጋሪነትን ስለሚጠየቅ ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አዘጋጅነት ”ሥነ-ምግባራዊ አመራር ለተቋም ግንባታ እና የሙስና መከላከል ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለጉራፈርዳ ወረዳ እና ለቢፍቱ ከተማ አስተዳደር አመራሮችናየመንግስተ3 ሠራተኞች በቢፍቱ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚነሸር ሙሉሰው ዘውዴ እንደተናገሩት የሙስና ተጽዕኖ ስልጣንን አለአግባብ ከመጠቀም በላይ…

Read More

የክልሉን የግብርና ምርታማነት ማነቆዎችን ለመፍታት እንዲቻል በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ ውጤታማ የምርምር ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተጠናቀቁ የግብርና ምርምር ተግባራት ሳይንሳዊ ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ዓለሙ ባደረጉት ንግግር ፣ኢንስቲትዩቱ የክልሉን የግብርና ምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን ለመፍታት እና የግብርና ዘርፍ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በምርምር ዘርፉ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ነው ብለዋል።…

Read More

ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሳተፋሉ

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ አለ፡፡ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 14 መርሐ ግብሮች እንዳሉት በሚኒስቴሩ የወጣቶች ብሔራዊ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፋፊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዐቢይ ኃ/መለኮት ተናግረዋል። የዳበረ የመደጋገፍ ዕሴትን ለማሳደግ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የላቀ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎን በማሳደግ አሠራሩን…

Read More

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ 1 ሺህ 85 ጣቢያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ከዛሬ ጀምሮ የሚሰጠውን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር አዲስ ፋና ትምህርት ቤት ተገኝተው አስጀምረዋል። በክልሉ ከ1ሺህ 86 በላይ የማስተፈኛ ጣቢያዎች መካከል ከ38 ሺህ 5 መቶ 93 በላይ ተማሪዎች በሰባት የትምህርት ዓይነቶች ፈተናውን እየተፈተኑ…

Read More

የክልሉን የታክስ አስተዳደርና የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑን የገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ለ114 የገቢ ተቋም ባለሙያዎች በሲግታክስ የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየተሠጠ ነው። የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ታደሰ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው ቢሮው የታክስ አስተዳደርና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን የዘመነ ለማድግ ከዚህ ቀደም ብዙ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል። ባለፋት ጊዜያት በሲግታክስ ተጠቅመን የግብር ግመታንና ውሳኔውን ለማውጣት…

Read More

አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ውጥረታቸውን ለማርገብ በለንደን እየመከሩ ነው

የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት በሁለቱ ልዕለ-ኃያላን ሀገራት መካከል የተፈጠረውን የንግድ ውጥረት ለማርገብ ዛሬ በእንግሊዝ ለንደን ለውይይት ተቀምጠዋል። በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን የንግድ ውጥረት ለማርገብ ባለፈው ወር በስዊዘርላንድ፣ ጄኔቫ ከተማ ሁለቱም ወገኖች አብዛኛውን ታሪፍ እንዲያነሱ ያስቻለ ቅድመ-ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ በአገራት ላይ ሊጥሉት ያቀዱትን ታሪፍ ለ90 ቀናት እንዲዘገይ ካሳወቁ በኋላ በአንጻሩ በቻይና…

Read More

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለክልሎች የሚከፋፈለው የጋራ ገቢ የድጎማ በጀት እያደገ መጥቷል፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለክልሎች የሚከፋፈለው የጋራ ገቢ የድጎማ በጀት እያደገ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። በውስን ዓላማ የድጎማ በጀቶች ትልልፍ እና በጋራ ገቢዎች ክፍፍል በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ የዳሰሳ ጥናት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የሀብት ክፍፍል ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን የምክር ቤቱ አፈ ጉብኤ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥ…

Read More