የመንግስት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍናን ለማሳደግ የሚያስችል የሪፎርም ትግበራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ በሪፎርም የሚካተቱ የክልል ቢሮዎች፣ ለዞን መምሪያ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲና በክልሉ ፍኖተ ካርታ ላይ የተዘጋጀ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እተሰጠ ይገኛል፡፡ የቢሮዉ ሃላፊ አቶ አስራት አዳሮ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸዉ፣የመንግስት የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ዓላማ የመንግስት ተቋማትን ቅልጥፍናና ዉጤታማነት፣ግልጽነት፣እና ተጠያቂነት በማሻሻል ቀልጣፋ ዉጤታማ…
